Quantcast
Channel: ርዕሰ አንቀጽ - Editorial
Browsing all 43 articles
Browse latest View live

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ኢትዮጵያን አትንኩ!!

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ተቋማት፣ ድርጅቶችና በአጠቃላይ ግለሰቦች ኢትዮጵያን የሚያገለግሉ እንጂ ከኢትዮጵያ በላይ አይደሉም፡፡

View Article



Image may be NSFW.
Clik here to view.

የኢሕአዴግ የራዕይ እጥረትና የተቃዋሚዎች ራዕይ አልባነት አገራችንን ለአደጋ ሊዳርጋት ይችላል

ኢትዮጵያችን ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ነው፡፡ ከምንም ጊዜም በላይ የመንግሥትን፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ የሕዝብን፣ የተቋማትን፣ የግል ዘርፉንና የሲቪል ማኅበረሰብን ትክክለኛ ራዕይና ጥንካሬ የሚጠይቅ ወቅት ነው፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ታላቅ የምስጋናና የክብር አቀባበል ለጀግኖች አትሌቶቻችን!

በለንደን ኦሊምፒክ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የአገር ጀግኖች ናቸው፡፡ ያሸነፉትም ያላሸነፉትም፡፡ ለውድድሩ የቀረቡትና የተዘጋጁት አገርን በመወከል ነውና፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

የኢትዮጵያ ሕዝብን በመርዛማ ጋዝ ለፈጀው ፋሽስት ጄኔራል ግራዚያኒ ሰሞኑን በጣሊያን ከተማ የክብር መታሰቢያ መናፈሻና...

የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ተቃውሞ ያስተጋባ! ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በጣሊያን አገር ከሮም ከተማ በስተደቡብ በምትገኝ አፊላ በምትባል መንደር፣ ለፊልድ ማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ የክብር መታሰቢያ ተብሎ የተገነባው የሕዝብ መናፈሻና ሙዚየም ከንቲባው በተገኙበት በክብርና በድምቀት ተመርቋል፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ሕዝብ ታላቅነትን መንግሥት በሳልነትን ያሳዩ!

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አረፉ የሚለውን ዜና የሰማ ሀቀኛ ኢትዮጵያዊና የኢትዮጵያ ወዳጅ ድንጋጤም ሐዘንም ተሰምቶታል፡፡ እኛም፡፡ ችግር ቢኖርም፣ ጉድለት ቢኖርም፣ እንደ ፖለቲካ ድርጅት መሪና እንደ አገር መሪ ታሪክ ለዘለዓለም በኩራት የሚያስታውሳቸው በርካታ አኩሪ ሥራዎችን ሠርተዋልና፡፡ ለአፍሪካም ጭምር፡፡

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

አድናቆት ምስጋናና ክብር ወርቅ ለሆነው ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

ወርቅ በእሳት ይፈተናል፡፡ በእሳት የሚፈተነው ግን የወርቅ ማዕድን ብቻ አይደለም፡፡ ወርቅ ሕዝብ ጭምር እንጂ፡፡ ወርቅ ሕዝብ፣ ጨዋ ሕዝብ፣ አስተዋይ ሕዝብ፣ ቅንና አገር ወዳድ ሕዝብ በችግርና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ይፈተናል፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ሕዝብ ለመንግሥት የቤት ሥራ ሰጥቷል ተግባራዊ ምላሽ ይጠበቃል!

ውል ክፍል መሄድ ሳያስፈልግና ቃለ ጉባዔ መፈራረም ሳይጠይቅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመንግሥት የቤት ሥራ ሰጥቷል፤ አደራ አቅርቧል፡፡ ተግባራዊ አዎንታዊ ምላሽም ከመንግሥት ይጠብቃል፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

እንደ አንድ ሕዝብ እንዳለቀስን እንደ አንድ ሕዝብ እንገስግስ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ታመሙ መባሉን እንደሰማ ለሁለት ወራት አዝኖና ደንግጦ፣ አረፉ መባሉን ከሰማ ወዲህም ለሁለት ሳምንት ሙሉ በመሪር ሐዘን በመዋጥ አልቅሶና ተላቅሶ፣ ነሐሴ 27 ቀን 2004 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትሩን አፍሪካና ዓለም በተገኙበት ብሔራዊ የቀብር ሥነ ሥርዓት ፈጽሞ ተሰናብቷል፡፡ እጅ እንነሳለን እንዳሉት...

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

ተጨማሪ ታሪክ እንሥራ! ዓለም እየጠበቀን ነው!

ወራሪዎችንና ቅኝ ገዥዎችን በማሸነፍ ታሪክ የምንሠራ ሕዝብ ብቻ ሳንሆን፣ አፍሪካዊያን ለነፃነት ሲታገሉ ከጐናቸው በመቆም ታሪክ የምንሠራ ሕዝብ ብቻ ሳንሆን፣ ክርስትናንና እስልምናን ከጥንቱ ከጠዋቱ በመቀበል ታሪክ የምንሠራ ሕዝብ ብቻ ሳንሆን፣

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

የኢትዮጵያ ሕዝብ የዘመንና የሥልጣን መሸጋገሪያ የግዴታ ስጦታ ከመንግሥት እየጠበቀ ነው

የዘንድሮ የዘመን መለወጫ በዓል ለየት ያለ ሆኗል፡፡ አሮጌው ዓመት አልፎ አዲስ ዓመት መምጣቱ የተለመደና ቤተሰብ መሰባሰቡ፣ እንኳን አደረሰህ መባባሉ፣ በጋራ መብላቱና መጫወቱ ባይቀርም፣ ዋናው አጀንዳ የዶሮ፣ የበግ፣ የመጠጥ፣ የጭፈራና የዘመን መቀያየር ሳይሆን፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕልፈት ምክንያት የተከሰተው የአመራር...

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ታሪክ ሥሩ እንድትከበሩ!

ከአፄ ገላውዴዎስ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በወግ በማዕረግ የመሪውን የቀብር ሥነ ሥርዓት ሲፈጽም ታሪክ አየን፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ጉዞአችን የመቀጠል ብቻ ሳይሆን የመጨመርም ይሁን

ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕልፈት በኋላ ያለውን ጉዞ በሚመለከት ከሁሉም በፊት የሚደቀነው ጥያቄ የተጀመረውን መቀጠል ይቻላል ወይ የሚል ነው፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ኢሕአዴግም ታሪክ ሠራ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዓለም ሕዝብ ታሪክ ሠርቶ አሳይቷል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሕልፈት ሲሰማ በጋራ አዘነ፤ በጋራ ተቆረቆረ፤ በሃይማኖትና በጐሳ የማይጋጭ ሕዝብ መሆኑን አስመሰከረ፡፡

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

ምረጥ! እጥፍ ድርብ ዕድገት ማስመዝገብ ወይስ እስካሁን የተመዘገበውን ዕድገት መነጠቅ

የኢትዮጵያ መንግሥት ዕድገታችን 11 በመቶ ነው ይበል፣ አይኤምኤፍ የለም ሰባት በመቶ ነው ይበል፣ ብዙ አያሳስበንም፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

የተፈጠረው አመቺ ሁኔታ እንዳያመልጠን

በአገራችን በመታየት ያለው መልካም ሁኔታ ለመልማትም ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባትም በእጅጉ አመቺ ነው፡፡

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

ዘለቄታዊ መፍትሔዎችን እያማተሩ ወቅታዊ ችግሮችንም መፍታት የግድ ይላል!

ከድህነት ለመላቀቅ፣ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ለመሰለፍ፣ ከጥገኝነት የተላቀቀ ኢኮኖሚ ለመገንባት፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን ዕውን ለማድረግ ሕገ መንግሥታዊ ግዴታው የሆነው መንግሥት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ተቃዋሚ ድርጅቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የብቃት ማረጋገጫ ሊያሳዩ ይገባል

በአንድ አገር የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመኖሩ አንዱ ማሳያ የተለያዩ አመለካከቶችና አማራጮች በኅብረተሰቡ ውስጥ ሲንሸራሸሩ ነው፡፡ ተራ መንሸራሸር ሳይሆን በተደራጀ ሁኔታ የእኔ ሐሳብ ከዚያኛው ሐሳብ ይበልጥ ለአገርና ለሕዝብ ይጠቅማል በሚል ይዘትና ቅርፅ ሲሰራጭ ነው፡፡ በፖለቲካ ድርጅት መልክና ቅርፅ፡፡

View Article


Image may be NSFW.
Clik here to view.

ኢትዮጵያን የዓለም የኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል እናድርጋት!

ኢትዮጵያችን ከአፍሪካ በቅኝ ገዥዎች ያልተገዛች አገር እየተባለች በዓለም ትታወቃለች፡፡ በጣም ጥሩ፡፡ ኢትዮጵያ ከሰማንያ በላይ ብሔር ብሔረሰቦች በሰላም የሚኖሩባት አገር ተብላም ትታወቃለች፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ብቃት ለሹመት!

ሹመት ስጦታ አይደለም፡፡ ሸክምና ኃላፊነት ነው፡፡ ሹመት ይህን ሥራ ምራበት እንጂ ፈንጭበት፣ ጋልብበት ተብሎ የሚሰጥ አይደለም፡፡ እዚህ ቦታ ላይ ተቀምጠህ ለፍትሕ ጥረህ ግረህ ሕዝብህን አገልግል፣ አገርህን ጥቀም ተብሎ የሚሰጥ ነው፡፡

View Article

Image may be NSFW.
Clik here to view.

ያልተከለሰና ያልተበረዘ የፕሬስ ነፃነት አሁኑኑ!!

የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ ሲባል ማንኛውም ተቋም፣ ማንኛውም ግለሰብ፣ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ሊጥሰው፣ ሊበርዘውና ሊከልሰው አይገባም ማለት ነው፡፡

View Article
Browsing all 43 articles
Browse latest View live




Latest Images